የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከኮቪድ ወረርሽኝ በፊት ወደ ነበረበት የሥራ ደረጃ ተመልሷል፦ አቶ መስፍን ጣሰው

5 Mons Ago
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከኮቪድ ወረርሽኝ በፊት ወደ ነበረበት የሥራ ደረጃ  ተመልሷል፦ አቶ መስፍን ጣሰው

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከኮቪድ ወረርሽኝ በፊት ወደ ነበረበት የሥራ ደረጃ ሙሉ በሙሉ መመለሱን የአየር መንገዱ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰው ገለጹ።

አየር መንገዱ አሁን ላይ የበረራ ተደራሽነቱን የበለጠ ለማሳደግ እየሠራ እንደሚገኝም ዋና ሥራ አስፈፃሚው ከአቪዬሽን ዴይሊ ጋር በነበራቸው ቆይታ ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ አሁን ላይ 140 በሚሆኑ አውሮፕላኖች እየሠራ መሆኑን ጠቅሰው፣ እ.አ.አ በ2035 የአውሮፕላኖቹን ቁጥር 271 ለማድረስ በዕቅድ እየተሠራ ነው ብለዋል።

ይህም ማለት በቀጣይ 12 ዓመታት አየር መንገዱ ቢያንስ 130 ተጨማሪ አውሮፕላኖች እንደሚኖሩት እና በዓመቱ መጨረሻ የቀጣይ ዙር የአውሮፕላን ትዕዛዞችን ለማድረግ መታሰቡን ገልጸዋል።

አየር መንገዱ ከቦይንግ 737 ማክስ እና ኤርባስ A320 ኒዮ በተጨማሪ 777X እና A350-1000 የተሰኙ አውሮፕላኖችን ወደ ሀገር ለማስገባት አቅዷል።

አየር መንገዱ በአሁኑ ጊዜ 29 አዳዲስ አውሮፕላኖችን ያዘዘ ሲሆን በያዝነው የበጀት ዓመትም 12 አዳዲስ አውሮፕላኖችን መቀበሉን አቶ መስፍን ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በፈረንጆቹ አቆጣጠር ሰኔ 2019 ላይ ከነበረው 12.2 ሚሊዮን የመንገደኞች ቁጥር ጋር ሲነጻጸር ዘንድሮ ከ13 ሚሊዮን በላይ መንገደኞችን ማስተናገዱንም ገልጸዋል።


ተያያዥ ርዕሶች

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top