አቶ ደመቀ መኮንን ከአሜሪካው አቻቸው ጋር በሳኡዲ አረቢያ ተወያዩ

5 Mons Ago
አቶ ደመቀ መኮንን ከአሜሪካው አቻቸው ጋር በሳኡዲ አረቢያ ተወያዩ

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ጋር ዛሬ ተወያይተዋል። አይኤስ አይኤስ የሽብር ቡድንን ለማጥፋት የተቋቋመው ዓለም አቀፍ ጥምረት የሚኒስትሮች ስብስባ ዛሬ በሳዑዲ አረቢያ ጅዳ ተካሄዷል። በስብስባው ላይ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን የተሳተፉ ሲሆን ከስብሰባው ጎን ለጎን ከአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ጋር ውይይት አድርገዋል። ውይይቱ ሁለቱ አገራት የሁለትዮሽ ትብብርን ማጠናከር በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይ፣ በሰላም ስምምነቱ ተፈጻሚነት፣ በሰሜን ኢትዮጵያ ክፍል ስላለው የሰብአዊ እርዳታ አቅርቦት፣ የሽግግር ፍትሕ ሂደት፣ የሰብአዊ መብቶች እና ሌሎች ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ መሆኑም ተገልጿል።


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top