በኮንስትራክሽን ሥራ ለመሠማራት የሚያበቃቸውን ሥልጠና ያጠናቀቁ የመጀመሪያ ዙር ባለሙያዎች ወደ ጀርመን ሊያቀኑ ነው

6 Mons Ago
በኮንስትራክሽን ሥራ ለመሠማራት የሚያበቃቸውን ሥልጠና ያጠናቀቁ የመጀመሪያ ዙር ባለሙያዎች ወደ ጀርመን ሊያቀኑ ነው

በኮንስትራክሽን ሥራ ለመሠማራት የሚያበቃቸውን ሥልጠና ያጠናቀቁ የመጀመሪያ ዙር ባለሙያዎች ወደ ጀርመን ሊሠማሩ መሆኑን የሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር አስታወቀ።

ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች በሲቭል ኢንጂነሪንግ፣ በኮንስትራክሽን ማናጅሜንት ቴክኖሎጂ፣ በአርክቴክቸር እና መሰል ሙያዎች የመጀመሪያ ዲግሪ ያላቸው ምሩቃን ወጣቶች ‘ጎተ’ በመባል በሚታወቀው የጀርመን ባህል እና ቋንቋ ኢንስቲትዩት ሥልጠናቸውን እየተከታተሉ ይገኛሉ።

ሥልጠናው ከዛሬ ሦሥት ዓመት በፊት በቀድሞው ከተማ ልማት እና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር እና የጀርመን ኮንስትራክሽን ማኅበራት ፌዴሬሽን በጋራ እንደተጀመረ ያብራሩት በሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር የሥራ፣ ሥራ ሥምሪት እና ገበያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ንጉሡ ጥላሁን ናቸው።

አቶ ንጉሡ በጎተ ባህል እና ቋንቋ ኢንስቲትዩት ሥልጠናቸውን አጠናቀው፣ የመጨረሻውን ምዘና አልፈው እና አስፈላጊውን የሥራ ትዕዛዝ ተቀብለው ወደ ጀርመን ሀገር ለመጓዝ ዝግጀታቸውን ያጠናቀቁ እንዲሁም በመሠልጠን ላይ ያሉ ምሩቃንን በሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር ግቢ አወያይተዋቸዋል።

በኢትዮጵያ የጀርመን ኮንስትራክሽን ማኅበራት ፌዴሬሽን ወኪል አቶ ኤልያስ አብዶ እንደገለጹት፣ ሥልጠናውን የሚከታተሉት ከተለያዩ ክልሎች የተውጣጡ ከ50 በላይ ሠልጣኞች ሲሆኑ፤ ሥልጠናውን ከጀመሩት መካከል 11ዱ ሥልጠናውን ካጠናቀቁ በኋላ የመጨረሻውን ፈተና በማለፍ የጀርመን ኮንስትራክሽን ፌዴሬሽን የሚፈልገውን መስፈርት አሟልተው ለጉዞ ዝግጁ የሆኑ ናቸው።

ሁሉንም ሂደቶች ካጠናቀቁት 11ዱ ሠልጣኞች ውስጥ 6ቱ ጀርመን ከሚገኙ አሠሪዎቻቸው ጋር የሥራ ውል የተፈራረሙ ሲሆን፤ የተቀሩትም የሥራ ውል ለመፈረም በመጠባበቅ ላይ መሆናቸውን ከሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል።


ተያያዥ ርዕሶች

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top