የፌደራል መንግሥት የ2016 ረቂቅ በጀት 801 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር እንዲሆን የሚኒስትሮች ምክር ቤት ውሳኔ አሳለፈ

5 Mons Ago
የፌደራል መንግሥት የ2016 ረቂቅ በጀት 801 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር እንዲሆን የሚኒስትሮች ምክር ቤት ውሳኔ አሳለፈ

የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 21ኛ መደበኛ ስብሰባ የ2016 በጀት ዓመት የፌደራል መንግሥት ረቂቅ የበጀት አዋጅ ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል።

የፌዴራል መንግስት የ2016 በጀት በአስር ዓመቱ መሪ የልማት ዕቅድ የተቀመጡ ግቦችን ታሳቢ በማድረግ፣ የሀገር ደህንነት ከማስጠበቅ፣ በተፈጥሮና በሰው ሰራሽ ችግሮች ምክንያት የተፈናቀሉ ዜጐችን ከመርዳት፣ በህግ ማስከበር ዘመቻው የወደሙ መሰረተ ልማቶች መልሶ ከማቋቋም፣ በቀጣይ ሊኖር የሚችለውን የማህበራዊና የኢኮኖሚ ትራንስፎርሜሽን አቅጣጫዎችና ዓላማዎች ከማሳካት አኳያ የተቃኘ ሲሆን የ2016 - 2020 የመካከለኛ ዘመን የማክሮ ኢኮኖሚ እና  የፊስካል ማዕቀፍን መሠረት  በማድረግ ተዘጋጅቶ የቀረበ ነው።

በዚሁ መሰረትም ለፌደራል መንግስት መደበኛ ወጪዎች ብር 369.6 ቢሊዮን፣ ለካፒታል ወጪዎች ብር 203.9 ቢሊዮን፣ ለክልሎች የሚሰጥ ድጋፍ ብር 214.07 ቢሊዮን፣ ለዘላቂ የልማት ግቦች ማስፈጸሚያ ድጋፍ ብር 14 ቢሊዮን በጠቅላላው ብር 801.65 ቢሊዮን ሆኖ ለምክር ቤቱ ቀርቧል።

ምክር ቤቱም በቀረበው የፌዴራል መንግሥት የ2016 በጀት ረቂቅ አዋጅ ላይ በስፋት ከተወያየ በኋላ ግብዓቶችን በማከል ወደ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ በሙሉ ድምጽ ወስኗል።


ተያያዥ ርዕሶች

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top