ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከኮሎምቢያ ምክትል ፕሬዚዳንት ፍራንሲያ ኢሌና ማርኩዌዝ ሚና ጋር ተወያዩ

6 Mons Ago
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከኮሎምቢያ ምክትል ፕሬዚዳንት ፍራንሲያ ኢሌና ማርኩዌዝ ሚና ጋር ተወያዩ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በኢትዮጵያ የሥራ ጉብኝት እያደረጉ የሚገኙት የኮሎምቢያ ምክትል ፕሬዚዳንት ፍራንሲያ ኢሌና ማርኩዌዝ ሚናን በጽቤታቸው ተቀብለው አነጋገሩ።

በውይይታቸው የሀገራቱ የሁለትዮሽ ግንኙነት በሚጠናከርበት ጉዳይ ላይ መክረዋል።

የኮሎምቢያ ምክትል ፕሬዚዳንት ፍራንሲያ ኢሌና ማርኩዌዝ ሚና የደቡብ ደቡብ ግንኙነትን ማጠናከር ላይ ፍላጎት እንዳላቸው የገለጹ ሲሆን ከኢትዮጵያ ጋር በኢኮኖሚ ትብብር እና ቱሪዝም ላይ በጋራ ለመሥራት በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ምክክር አድርገዋል።

ኮሎምቢያ እና ኢትዮጵያ የሁለትዮሽ ግንኙነትን ለማጠናከር የሚያስችል የመግባቢያ ሰነድ በትናንትናው ዕለት የተፈራረሙ ሲሆን ምክትል ፕሬዚዳንቷ ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ጋር መምከራቸው ይታወሳል።

በሮዛ መኮንን


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top