የቱርክ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ በድጋሚ ሊካሄድ ነው

11 Mons Ago
የቱርክ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ በድጋሚ ሊካሄድ ነው

በቱርክ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ 50 በመቶ በላይ ውጤት ያስመዘገበ ተመራጭ ባለመኖሩ ምርጫው በድጋሚ ሊካሄድ ነው።

የድምፅ ቆጠራው እየተካሄደ ባለው የቱርክ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ላለፉት 20 ዓመታት ሀገሪቱን የመሩት ረሲፕ ጠይብ ኤርዶጋን ብርቱ ፉክክር ገጥሟቸዋል።

በምርጫው ለማሸነፍ ከ50 መቶ በላይ ማስመዝገብ ግዴታ ሲሆን፤ እስካሁን በተደረገው ቆጠራ 49.5 በመቶ የሚሆነውን ድምፅ በማግኘት ፕሬዝዳንት ኤርዶጋን እየመሩ ነው።

ተፎካካሪያቸው ከማል ክሊቻሮግሉ ደግሞ 44.89 በመቶ የሚሆነውን አግኝተዋል።

የቆጠራ ሂደቱ 99.87 በመቶ እንደተጠናቀቀም ቲ አር ቲ ወርልድ እና አናዶሉ እየዘገቡ ይገኛሉ።

ሁለቱም ተፎካካሪዎች ሀገር ለመምራት የሚያስችል ከ50 በመቶ በላይ ውጤት ማስመዝገብ ባለመቻላቸው ድጋሚ ምርጫ ግንቦት 20 ይካሄዳል ተብሎ ይጠበቃል።

ከምርጫው አስቀድሞ ሁለቱም ተፎካካሪዎች እንደሚያሸንፉ ተናግረው የነበረ ሲሆን፤ አሁን ደግሞ ከማል ክሊቻሮግሉ በድጋሚ ምርጫው ብልጫ እንደሚወስዱ እየገለጹ ይገኛሉ።


ተያያዥ ርዕሶች

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top