የፈረንሳይ መንግሥት የአብአላ ሆስፒታልን መልሶ ለመገንባት የሚያስችል የ2.5 ሚሊዮን ዩሮ ድጋፍ ለማድረግ የመግባቢያ ስምምነት ፈረመ

7 Mons Ago
የፈረንሳይ መንግሥት የአብአላ ሆስፒታልን መልሶ ለመገንባት የሚያስችል የ2.5 ሚሊዮን ዩሮ ድጋፍ ለማድረግ የመግባቢያ ስምምነት ፈረመ

የፈረንሳይ መንግሥት በአፋር ክልል የሚገኘውን የአብአላ ሆስፒታል መልሶ ለመገንባት የሚያስችል የ2.5 ሚሊዮን ዩሮ ድጋፍ ለማድረግ ከጤና ሚኒስቴር ጋር የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርሟል።

ሆስፒታሉ ከ300 ሺህ በላይ ለሚሆኑ የአካባቢው ነዋሪዎች አገልግሎት ሲሰጥ የቆየ ሲሆን በሰሜኑ ጦርነት ምክንያት ከፍተኛ ጉዳት እንደደረሰበት ተገልጿል።

የፈረንሳይ መንግሥት የሚያደርገው ድጋፍ ሆስፒታሉን መልሶ ከመገንባት ባለፈ አገልግሎቱን ለማሻሻል እንደሚያግዘው የጤና ሚኒስትሯ ዶ/ር ሊያ ታደሰ ገልጸዋል።

ስምምነቱን ከጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ ጋር የተፈራረሙት በኢትዮጵያ የፈረንሳይ አምባሳደር ሬሚ ማርሾው በበኩላቸው፣ በትግራይ፣ አፋር እና አማራ ክልሎች በጦርነቱ ጉዳት የደረሰባቸውን የጤና ተቋማት እና በአካባቢው ያሉ ነዋሪዎችን ለመደገፍ ረገድ የሚደረገው ጥረት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ጠቁመዋል።

የመግባቢያ ስምምነቱ ከዚህ በፊት ቃል በተገባው መሠረት እንደሚፈፀም እና የመልሶ የማቋቋም ሥራውም በ2 ዓመት ውስጥ የሚተገበር መሆኑንም ተናግረዋል።

በዓለም ይልፉ


ተያያዥ ርዕሶች

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top