የትምህርት ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ከብሪታኒያ የልማትና የአፍሪካ ጉዳዮች ሚኒስትር ዴኤታ አንድሪው ሚቼል ጋር መከሩ።
በውይይታቸውም ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) በኢትዮጵያ በትምህርቱ ዘርፍ እየተከናወኑ የሚገኙ የማሻሻያ ስራዎችን አብራርተዋል።
ኢትዮጵያ ለትምህርት ጥራት ትኩረት ሰጥታ እየሰራች መሆኑን ነው ሚኒስትሩ የተናገሩት።
ሁለቱ አካላት በዘርፉ የሚስተዋሉ ተግዳሮቶችን አንስተው በትኩረት መምከራቸውን በብሪታኒያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ ያመላክታል።
አንድሪው ሚቼል፣ ብሪታኒያ የሴቶች ትምህርት ሊሻሻል በሚችልበት ጉዳይ ላይ ከኢትዮጵያ ጋር በቅርበት ለመሥራት ዝግጁ መሆኗን ተናግረዋል።