የካፒታል ገበያ ሲተገበር በኢትዮጵያ የፋይናንስ ሥርዓት ላይ ተጨባጭ ለውጥ የሚያመጣ መሆኑን የቻርተርድ ኢንስቲትዩት ፎር ሴኪዩሪቲስ ኤንድ ኢንቨስትመንት ኤክስፐርት ሳንዲ ራይት ገለጹ።

11 Mons Ago
የካፒታል ገበያ ሲተገበር በኢትዮጵያ የፋይናንስ ሥርዓት ላይ ተጨባጭ ለውጥ የሚያመጣ መሆኑን የቻርተርድ ኢንስቲትዩት ፎር ሴኪዩሪቲስ ኤንድ ኢንቨስትመንት ኤክስፐርት ሳንዲ ራይት ገለጹ።
መቀመጫውን ለንደን ያደረገው የተለያዩ አገራት የካፒታል ገበያዎች ላይ የባለሙያዎች ስልጠናና የአቅም ማጎልበቻ ድጋፍ የሚሰጠው 'ቻርተርድ ኢንስቲትዩት ፎር ሴኪዩሪቲስ ኤንድ ኢንቨስትመንት' ከኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለሥልጣን ጋርም በቅንጅት እየሰራ ይገኛል።
የካፒታል ገበያ አክሲዮን፣ ቦንድ፣ ተዛማጅ ውሎች የመሳሰሉ ሰነድ መዋዕለ ንዋዮች ግብይት የሚከናወንበት ቦታ ነው።
ባደጉት አገራት በስፋት የሚታወቀውን የካፒታል ገበያን በኢትዮጵያ ወደ ስራ ለማስገባት አዋጅ 1248/2013 ጸድቆና የካፒታል ገበያ ባለስልጣን ተቋቁሞ በሂደት ላይ ይገኛል።
የ'ቻርተርድ ኢንስቲትዩት ፎር ሴኪዩሪቲስ ኤንድ ኢንቨስትመንት' ባለሙያ ሳንዲ ራይት፤ ኢትዮጵያ የካፒታል ገበያን ለመጀመር እያደረገች ያለውን እንቅስቃሴ አድንቀዋል።
"ኢትዮጵያ የካፒታል ገበያን ለመጀመር እያደረገች ያለችው ዝግጅት ሌሎች ልምድ ካላቸው አገራት ጋር እኩል ደረጃ ላይ ሊያስቀምጣት የሚችል ነው ብለዋል"።
የካፒታል ገበያ በተለይም በቅርቡ የሚተገበረው የኢትዮጵያ ሰነድ መዋዕለ ንዋዮች ገበያ ጋር ተዳምሮ ኢንቨስትመንትን በማስፋፋት ከውጭ የሚመጣ የገንዘብ አቅምን በማጠናከርና ቁጠባን በማሳደግ ረገድ ወሳኝ ጠቀሜታ እንዳለው ገልጸዋል።
በመሆኑም የካፒታል ገበያ ወደ ስራ ሲገባ በኢትዮጵያ የፋይናንስ ስርዓት ትልቅ ለውጥ ያመጣል ነው ያሉት።
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የንግድ ስራ ኮሌጅ የአካውንቲንግና ፋይናስ መምህርና የካፒታል ገበያ ፕሮጀክት አስተባባሪ ታምራት መንገሻ፤ የካፒታል ገበያ በኢኮኖሚው በቂ የገንዘብ ዝውውር እንዲኖር እንደሚያስችል ገልጸዋል።
እንደ ሳንዲ ራይትና መምህር ታምራት መንገሻ ገለጻ፤የካፒታል ገበያው ተአማኒነትን፣ ግልፅነትን፣ ብቃትና ቅልጥፍናን የሚፈልግ ለዚህም ጠንካራ የቁጥጥር ማዕቀፍ፣ ገበያውን የሚያሳልጥ ብቁ የሰው ኃይል፣ቴክኖሎጂና ሌሎች መሰረተ ልማቶችን ማሟላት ያስፈልጋል።
እንደ ኢዜአ ዘገባ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲና 'ቻርተርድ ኢንስቲትዩት ፎር ሴኪዩሪቲስ ኤንድ ኢንቨስትመንት' ከኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን ጋር በመሆን ገበያውን መጀመር የሚያስችል የባለሙያዎች ስልጠና እየሰጡ ነው

ተያያዥ ርዕሶች

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top