ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በግርማ የሺጥላ ህልፈት የተሰማቸውን ሃዘን ገለጹ

7 Mons Ago
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በግርማ የሺጥላ ህልፈት የተሰማቸውን ሃዘን ገለጹ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የአማራ ክልል ብልጽግና ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ የነበሩት አቶ ግርማ የሺጥላ ህልፈት የተሰማቸውን ሃዘን ገልጸዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት የሀዘን መግለጫ፣ “ሐሳብን በሐሳብ ማሸነፍ ያቃታቸው አካላት የወንድማችንን የአቶ ግርማ የሺጥላን ነፍስ ነጥቀዋል” ብለዋል።
ልዩነትን በሠለጠነ መንገድ መፍታት ባህል በሆነበት ክፍለ ዘመን፣ በሐሳብ የተለየንን ሁሉ በጠመንጃ ለማሳመን መነሣት የጽንፈኝነት የመጨረሻው ጥግ ነው ሲሉም ገልጸዋል።
ተወልዶ ባደገበት አካባቢ፣ ከእኛ የተለየ ሐሳብ ማሰብ አልነበረበትም ብለው የሚያምኑ ነውጠኛ ጽንፈኞች የፈጸሙት አስነዋሪና አሰቃቂ ተግባር መሆኑን አንስተዋል።
ጽንፈኝነትን በጊዜ ታግለን ካላስወገድነው ወደ መጨራረስ እንደሚወስደን ጉልሕ ማሳያ ነው ሲሉም አጽንኦት ሰጥተዋል።
በስተመጨረሻም፣ የአቶ ግርማ የሺጥላ ነፍስ በሰላም ታርፍ ዘንድ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሀዘናቸውን ገልጸዋል።

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top