በአራት የአፍሪካ ሀገራት ጉብኝት እያደረጉ ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስተር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን አራተኛ ሀገር ጉብኝታቸውን በኡጋንዳ ማድረግ ጀምረዋል።
አቶ ደመቀ ኡጋንዳ ሲደርሱ የሀገሪቱ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ሄነሪ ኦኬሎ አቀባበል አድርገውላቸዋል።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በኡጋንዳ ቆይታቸው ከሀገሪቱ ፕሬዝደንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ ጋር በሁለትዮሽ እና አካባቢያዊ ጉዳዮች ላይ ይመክራሉ ተብሎ ይጠበቃል።
እንዳሁም በኡጋንዳ እየተካሄደ በሚገኘው የሶማሊያ ሰላም ማስከበር ተልዕኮ ሠራዊት ያበረከቱ ሀገራት ጉባኤ ላይ የሚሳተፉ እንደሚሆን ከውጭ ጉዳይ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።