“በሰሜን ኢትዮጵያ የነበረው ውጥረት ረግቦ ሰላም እንዲሰፍን የሔድንበት መንገድ ውጤታማ ነው” - ኦሊሴንጎን ኦባሳንጆ

7 Mons Ago
“በሰሜን ኢትዮጵያ የነበረው ውጥረት ረግቦ ሰላም እንዲሰፍን የሔድንበት መንገድ ውጤታማ ነው” - ኦሊሴንጎን ኦባሳንጆ
በኢፌዴሪ መንግሥት እና በህወሓት መካከል የነበረውን ውጥረት ለማርገብ የሄድንበት መንገድ ውጤታማ ነው ሲሉ የናይጀሪያ የቀድሞ ፕሬዚዳንትና የአፍሪካ ሕብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ኦሉሴጉን ኦባሳንጆ ገለጹ።
በአዲስ አበባ ከተማ ወዳጅነት አደባባይ 'ጦርነት ይብቃ፤ ሰላም እናጽና’ በሚል መሪ ሐሳብ የምስጋና እና የዕውቅና ሥነ ስርዓት እየተካሔደ ነው።
በፈረንጆቹ የዘመን ቀመር ገና ለዚህ የሰላም ማስፈን ሥራ ስሰለፍ ውጥረቱ ረግቦ ሰላም እንደሚሰፍን ሙሉ ተስፋ ነበረኝ ብለዋል በንግግራቸው።
በኢትዮጵያ መንግስትም ሆነ በህወሓት በኩል ለሰላም ሂደቱ መሳካት የነበረው አዎንታዊ አቀባበል ለሰላም ማስፈን የተደረገውን ጥረት በእጅጉ ያገዘ እንደነበርም በአጽንኦት ገልጸዋል።
የሰላም ሂደቱን ተከትሎ የኢትዮጵያ መንግስት ስምምነቱን ተግባራዊ ለማድረግ ያሳየውን ቁርጠኛነት አድንቀው፣ ለስምምነቱ ውጤታማነት እና ዘላቂነት ትልቅ ማሳያ ስለመሆኑም ነው የተናገሩት።
በጠፋው ሕይወት ብናዝንም ነገር ግን በተገኘው ሰላም ደግሞ ደስታችንን እንገልፃለን ብለዋል።
በተጨማሪም የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽነር፣ የቀድሞ የኬንያ ፕሬዚዳንት አሁሩ ኬኒያታ፣ የደቡብ አፍሪካ ፕረዚዳንት ራማፎሳ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትራቸው ለሰላም ስምምነቱ ያደረጉትን ጥረት እንደሚያደንቁ ኦባሳንጆ ተናግረዋል።
በሰላም ስምምነቱ መሠረት የተከናወኑ ሥራዎች እንደተጠበቁ ሆነው ቀሪ ሥራዎችም በፍጥነት እንዲፈጸሙ ጠይቀዋል።

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top