ሀገራችን ፋታ ትፈልጋለች፤ ህዝባችንም ሰላምና ብልጽግና ይሻል - አቶ ደመቀ መኮንን

7 Mons Ago
ሀገራችን ፋታ ትፈልጋለች፤ ህዝባችንም ሰላምና ብልጽግና ይሻል -  አቶ ደመቀ መኮንን
ሀገራችን ፋታ ትፈልጋለች ፤ ህዝባችንም ሰላምና ብልጽግና ይሻል ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ተናገሩ።
ለአፍሪካ ችግር አፍሪካዊ መፍትሔ መልካም ሂደት ላይ ይገኛል ያሉት አቶ ደመቀ፣ 'እኔ ያልኩት ካልሆነ' እልህ ብዙ ዋጋ አስከፍሎናል፤ ለዚህም ከታሪክ ሳይሆን ከተግባር ተምረናል ብለዋል።
የዛሬው መርሐ ግብር ከዚህ ስሁት መንገድ ወጥተን ለሰላም ጥረት ያደረጉትን ወገኖች ለማመስገን መሆኑን የገለጹት አቶ ደመቀ፣ የየዕለት ተግባራችን ህዘቡን ሰላም የሚያስጠብቅ መሆን እንዳለበት አሳስበዋል።
አቶ ደመቀ እንደተናገሩት፣ የሁሉንም ድምጽ አድምጠን በልኩ ምላሽ እየሰጠን መሄድ አለብን፤ በግጭት የሚነሳውን ስማችንን አድሰን ከጎናችን ለነበሩት አፍሪካውያን ወንድሞቻችን አርአያ መሆን አለብን ብለዋል።
ከአውዳሚው ጦርነት ወደ ሰላማዊ አውድ ለመምጣት ለአፍሪካዊ ችግር አፍሪካዊ መፍትሔ ስኬት የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ላበረከቱ ሁሉ ምስጋና አቅርበዋል።

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top