በወንጀል ተጠርጥረው ክስ ቀርቦባቸው የነበሩ የህወሓት ሲቪል እና ወታደራዊ አመራሮች ክስ ተቋረጠ

1 Yr Ago
በወንጀል ተጠርጥረው ክስ ቀርቦባቸው የነበሩ የህወሓት ሲቪል እና ወታደራዊ አመራሮች ክስ ተቋረጠ
በወንጀል ተጠርጥረው ክስ ቀርቦባቸው የነበሩ የህወሓት ሲቪል እና ወታደራዊ አመራሮች ክስ መቋረጡን የፍትህ ሚኒስቴር አስታወቀ።
በፌዴራል መንግስት እና በህዝባዊ ወያነ ሃርነት ትግራይ (ህወሓት) መሃከል በተፈረመው የሰላም ስምምነት መሰረት ከግጭቱ ጋር ተያያዥ የሆኑ ወንጀሎች ተጠያቂነት በተመለከተ ያለውን ዓለም አቀፍ ተሞክሮ ታሳቢ ባደረገ መልኩ በሽግግር ፍትህ ማዕቀፍ ሊታዩ እንደሚገባ ስምምነት ላይ መደረሱን ሚኒስቴሩ ገልጿል።
ስለሆነም በወንጀል ተጠርጥረው ክስ ቀርቦባቸው የነበሩ የህዝባዊ ወያነ ሃርነት ትግራይ ሲቪል እና ወታደራዊ አመራሮችን ክስ በማቋረጥ ጉዳያቸው በቀጣይ በሽግግር ፍትህ ማዕቀፍ እንዲታይ ማድረግ አስፈላጊ ሆኖ መገኘቱን የፍትህ ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።
ስለዚህ በተገለፀው አግባብ ከዚህ ጋር በተያያዘ ክስ ቀርቦባቸው በክርክር ሂደት ላይ ይገኙ የነበሩ የወንጀል ክሶች በአዋጅ 943/2008 አንቀጽ 6 (3) (ሠ) መሰረት የተነሱ መሆኑን ሚኒስቴሩ አስታውቋል።

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top