ምክር ቤቱ በህወሓት ላይ አሳልፎ የነበረውን የሽብርተኝነት ውሳኔ አነሳ

1 Yr Ago 550
ምክር ቤቱ በህወሓት ላይ አሳልፎ የነበረውን የሽብርተኝነት ውሳኔ አነሳ
የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሕዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ከሽብርተኛ ድርጅት እንዲሠረዝ ውሳኔ አሳለፈ።
ምክር ቤቱ ዛሬ ባካሄደው ልዩ ጉባኤው ነው ከሁለት አመታት በፊት በህወሓት ላይ ተጥሎ የነበረውን የሽብርተኝነት ወንጀል ያነሳው።
ከ2 ዓመት በፊት በሰሜኑ የሃገራችን ክፍል በተቀሰቀሰው አለመረጋጋት ምክንያት የሽብር ወንጀልን ለመከላከልና ለመቆጣጠር በወጣው አዋጅ ቁጥር 1176/2012 አንቀጽ 20 ንኡስ አንቀጽ 2 መሠረት የሚኒስትሮች ምክር ቤት ሚያዚያ 23 ቀን 2013 ዓ.ም ባካሄደው 23ኛ አስቸኳይ ስብሰባ ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) እና “ሸኔ’’ ድርጅቶች በሽብርተኝነት እንዲሰየሙ የውሳኔ ሃሳብ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አቅርቦ ምክር ቤቱ እንዳጸደቀው ይታወሳል።
በጉዳዩ ላይ የምክር ቤቱ አባላት የተለያዩ ጥያቄዎችን ያነሱ ሲሆን በመጨረሻም ህወሓትን ከሽብርተኝነት ዝርዝር ለማውጣት የቀረበውን የውሳኔ ሀሳብ በ61 ተቃውሞ እና በ5 ድምፀ ተአቅቦ በአብላጫ ድምጽ ጸድቋል።
በተስፋዬ ጫኔ

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top