ዋልያዎቹ የመጀመሪያ ልምምዳቸውን በኢቢሲ የሚዲያ ኮምፕሌክስ ሜዳ አካሄዱ

8 Mons Ago
ዋልያዎቹ የመጀመሪያ ልምምዳቸውን በኢቢሲ የሚዲያ ኮምፕሌክስ ሜዳ አካሄዱ
የ2023ቱ የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ከጊኒ ጋር የደርሶ መልስ ጨዋታ ያለበት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዛሬ የመጀመሪያ ልምምዱን በአዲሱ የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን /ኢቢሲ/ የሚዲያ ኮምፕሌክስ ሜዳ አካሄደ።
ብሔራዊ ቡድኑ በኢቢሲ ሜዳ ልምምዱን ሲያደርግ የተገኙት የኢቢሲ ም/ዋና ሥራ አስፈፃሚ እና የቴሌቪዥን ዘርፍ ኃላፊ ወ/ሮ ሀቢባ ፋሪሰ፤ ም/ዋና ሥራ አስፈፃሚ እና የሬዲዮ ዘርፍ ኃላፊ ዶ/ር ያኒያ ሰኢድ እንዲሁም ም/ዋና ሥራ አስፈፃሚ እና የሥልጠና ማዕከል ኃላፊ አቶ ታደሰ በላቸው የእንኳን ደህና መጣችሁ አቀባበል አድርገውላቸዋል።
ቡድኑ በኢቢሲ ሜዳ በፈለገው ጊዜ ልምምዱን ማድረግ እንደሚችል ተናግረው፣ በቀጣይ ላለባቸው ጨዋታ መልካም ውጤት ተመኝተዋል።
አሠልጣኝ ውበቱ አባተ በበኩላቸው፣ በኢቢሲ ይህን ዓይነት ሜዳ ማየታቸው እንዳስገረማቸው ገልጸው ለተደረገላቸው አቀባበልም አመስግነዋል።
ከጊኒ ጋር መጋቢት 15 እና 18/2015 ዓ.ም የሚጫወተው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በሀገር ውስጥ ከሚያደርገው ልምምድ በተጨማሪ በመጪው እሑድ ከሩዋንዳ ብሔራዊ ቡድን ጋር በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ሜዳ የወዳጅነት ጨዋታ ያካሂዳል።
በንዋይ ይመር

ተያያዥ ርዕሶች

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top