የኬንያ ወታደሮች 7 የአልሻባብ ታጣቂዎችን መግደላቸውን አስታወቁ

3 Yrs Ago
የኬንያ ወታደሮች 7 የአልሻባብ ታጣቂዎችን መግደላቸውን አስታወቁ

ታህሳስ 24፡ 2011 ዓ.ም

በደቡብ ሶማሊ የሚገኙ 7 የአልሻባብ ታጣቂዎችን መግደላቸውን የኬንያ ወታደሮች አስታወቁ፡፡

የኬንያ መከላከያ ሀይል ቃል አቃባይ የሆኑት ፖል ኒጁግና በመግለጫቸው እንዳስታወቁት በአሚሶም ትዕዛዝ የኬንያ መከላከያ ሀይል የአልሻባብ ድንበር የሆነውን ታብዳ ዴላሁላን መደብደባቸውን አስታውቀዋል፡፡

በድብደባው ተጨማሪ የአልሻባብ ታጣቂዎች መሞታቸው ተገልጿል፡፡

የኬንያ ወታደሮች ኤኬ 47 ጠመንጃ እና 2 የሮኬት ፈንጂ እንዲሁም 10 ተቀጣጣይ ፈነጂዎች መማረካቸውን ገልፀዋል፡፡

ምንጭ፤ አናዱሉ

ግብረመልስ
Top