አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ለ23 ተጫዋቾች ጥሪ አቀረቡ

18 Days Ago
አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ለ23 ተጫዋቾች ጥሪ አቀረቡ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ዉበቱ አባተ ከጊኒ ጋር ለሚያደርጉት የአፍሪካ ዋንጫ ጨዋታ ለ23 ተጫዋቾች ጥሪ አድርገዋል፡፡
በዚህም ግብ ጠባቂ ፋሲል ገብረ ሚካኤል ከባህርዳር ከነማ ፣ ሰዒድ ሃብታሙ ከአዳማ ከነማ እና አቡበከር ኑራ ከኢትዮጵያ መድን ተመርጠዋል፡፡
በተከላካይ ክፍል፣ ረመዳን የሱፍ ከቅዱስ ጊዮርጊስ፣ ብርሀኑ በቀለ ከሀዲያ ሆሳዕና፣ ሱሌይማን ሀሚድ ከቅዱስ ጊዮርጊስ፣ ሚሊዮን ሰለሞን ከአዳማ ከተማ፣ ምኞት ደበበ ከቅዱስ ጊዮርጊስ፣ ጊት ጋትኩት ከሲዳማ ቡና፣ አስቻለው ታመነ ከፋሲል ከነማ እና ያሬድ ባዬ ከባህር ዳር ከተማ ተመርጠዋል፡፡
በመሀል ክፍል ተጫዋች፣ ይሁን እንዳሻው ከፋሲል ከነማ፣ አማኑኤል ዮሐንስ ከኢትዮጵያ ቡና፣ ጋቶች ፓኖም ከቅዱስ ጊዮርጊስ፣ ሽመልስ በቀለ ከኤንፒ፣ ከነዓን ማርክነህ ከመቻል፣ ታፈሰ ሰለሞን ከፋሲል ከነማ እና ቢኒያም በላይ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ተመርጠዋል፡፡
በአጥቂ ክፍል ዮሴፍ ታረቀኝ ከአዳማ ከተማ፣ አቤል ያለው ከቅዱስ ጊዮርጊስ፣ ዑመድ ዑኩሪ ከአል ሱዋይቅ፣ ይገዙ ቦጋለ ከሲዳማ ቡና እና አቡበከር ናስር ከማሜሎዲ ሰንዳውንስ መመረጣቸውን ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ተያያዥ ርዕሶች

ግብረመልስ
Top