በአቶ አህመድ ሽዴ የተመራው የኢትዮጵያ ልዑክ የአሊባባ ግሩፕ ዋና መስሪያ ቤትን ጎበኘ

9 Mons Ago
በአቶ አህመድ ሽዴ የተመራው የኢትዮጵያ ልዑክ የአሊባባ ግሩፕ ዋና መስሪያ ቤትን ጎበኘ
በገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ የተመራው የኢትዮጵያ ልዑክ በቤጂንግ የሚገኘውን የአሊባባ ግሩፕ ዋና መስሪያ ቤትን ጎብኝቷል።
ልዑኩ የተቋሙን ታሪክ፣ የእድገት ሂደት እና የወደፊት ትንበያ የሚያስቃኘውን የኤግዚቢሽን አዳራሽ ተዘዋውሮ ተመልክቷል።
ልዑኩ ከጉብኝቱ በተጨማሪ በኢትዮጵያ እና በአሊባባ ግሩፕ መካከል በኢ-ኮመርስ እና በዲጂታል ኢኮኖሚ ዘርፎች ወደፊት ስለሚደረገው ትብብር
ከተቋሙ ምክትል ፕሬዝዳንት ሚስተር ሊዩ ናን እና ከሌሎች አመራሮች ጋር ፍሬያማ ውይይት ማድረጉን በቤጂንግ የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ አመልክቷል።

ተያያዥ ርዕሶች

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top