"የአድዋ ዜሮ ዜሮ ፕሮጀክት በመጭው ጥቅምት ሙሉ በሙሉ ተጠናቆ ወደ ስራ ይገባል" - የአዲስ አበባ የትላልቅ ፕሮጀክቶች ግንባታ ጽህፈት ቤት

9 Mons Ago
"የአድዋ ዜሮ ዜሮ ፕሮጀክት በመጭው ጥቅምት ሙሉ በሙሉ ተጠናቆ ወደ ስራ ይገባል" - የአዲስ አበባ የትላልቅ ፕሮጀክቶች ግንባታ ጽህፈት ቤት
የአድዋ ዜሮ ዜሮ ፕሮጀክት ጥቅምት ተጠናቆ ሙሉ በሙሉ ወደ ስራ እንደሚገባ የአዲስ አበባ የትላልቅ ፕሮጀክቶች ግንባታ ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡፡
የጽህፈት ቤቱ የኮንትራት አስተዳደር ዳይሬክተር ኢንጂነር ዳዊት ጥበቡ በተለያዩ ውጣውረዶች ውስጥም ቢሆን ፕሮጀክቱን 78 ነጥብ 2 በመቶ ማድረስ ተችሏል ብለዋል፡፡
በተያዘለት ጊዜ እንዲጠናቀቅም በከፍተኛ ተሳትፎ ስራዎች እየተሰሩ መሆናቸውን ዳይሬክተሩ ተናግረዋል፡፡
ፕሮጀክቱ መስከረም 19/2012 ዓ.ም መጀመሩ የሚታወስ ሲሆን በውስጡ ሙዚየም ፣ ምክር ቤት እና 3 የመሰብሰቢያ አዳራሾች ፣ መዝገብ ቤት እና ቤተ መጻሕፍት ፣ አምፊ ቲያትር፣ ፏፏቴዎች፣ ኤግዚቢሽኖች እና የስነ ጥበብ ጋለሪን ያካተተ ነው፡፡
በአሸናፊ እንዳለ

ተያያዥ ርዕሶች

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top