ኢትዮጵያ እና ቻይና የኢንቨስትመንት እና የኢኮኖሚ ትብብራቸውን ለማሳደግ የሚያስችል ቡድን ለመመሥረት ስምምነት ተፈራረሙ

9 Mons Ago
ኢትዮጵያ እና ቻይና የኢንቨስትመንት እና የኢኮኖሚ ትብብራቸውን ለማሳደግ የሚያስችል ቡድን ለመመሥረት ስምምነት ተፈራረሙ
ኢትዮጵያ እና ቻይና የኢንቨስትመንት እና የኢኮኖሚ ትብብራቸውን ለማሳደግ የሚያስችላቸውን የትግበራ ቡድን ለመመሥረት በዛሬው ዕለት የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ ተፈራርመዋል።
ስምምነቱን ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት ቻይና ቤጂንግ የገቡት የኢፌዴሪ ገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አሕመድ ሺዴ እና የቻይና የንግድ ሚኒስቴር ረዳት ሚኒስትር ሊ ፌይ መፈራረማቸውን በቻይና የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስታውቋል።
ቡድኑ የሁለቱን ሀገራት የሁለትዮሽ ኢኮኖሚያዊ እና የንግድ ግንኙነታቸውን በስትራቴጂካዊ መስኮች በጋራ የማሳደግ ዓላማን ያነገበ መሆኑ ተገልጿል።
በገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አሕመድ ሺዴ የተመራ ልዑክ ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት ቤጂንግ መግባቸው ይታዋል።
ልዑኩ በኢትዮጵያ እና ቻይና የንግድ፣ ኢንቨስትመንት እና ኢኮኖሚ ትብብር ጉዳዮች ላይ ትኩረት ያደረገ ውይይት በማድረግ ላይ ይገኛል።

ተያያዥ ርዕሶች

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top