የምንፈልጋትን ኢትዮጵያን ለመፍጠር በልጆች ላይ መሥራት ይገባል፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ

1 Yr Ago
የምንፈልጋትን ኢትዮጵያን ለመፍጠር በልጆች ላይ መሥራት ይገባል፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ
የምንፈልጋትን ኢትዮጵያን ለመፍጠር በልጆች ላይ መሥራት እንደሚገባ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ገለጹ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 ሳር ቤት አካባቢ እንደ አዲስ የተገነባ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራን ሥራ አስጀምረዋል።
ስመ ጥር ስፖርተኞችን ለመፍጠር በስፖርት ማዘውተሪያዎች ላይ መሥራት እንደሚገባም ተናግረዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትሥሥር ገጻቸው ባሰፈሩት መልእክት “በአካል፣ በሥነ-ምግባር እና በሥነ-ልቡና የዳበረ ትውልድ ለመፍጠር የሚያግዘንን የስፖርት ማዘውተሪያ ገንብተናል።” ብለዋል።
የአካባቢው ተመሳሳይ የስፖርት ማዕከላትን እያስፋፋን እንቀጥላለን፤ ነገ የምንፈልጋትን ሀገር ለመገንባት በዛሬው ትውልድ ላይ መሥራት ይኖርብናል።” ሲሉም አክለዋል።

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top