"ኢትዮጵያ ‘ለአፍሪካ ችግር አፍሪካዊ መፍትሄ' የሚለውን መርህ በተግባር ተጠቅማበታለች" - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ

9 Mons Ago
"ኢትዮጵያ ‘ለአፍሪካ ችግር አፍሪካዊ መፍትሄ' የሚለውን መርህ በተግባር ተጠቅማበታለች" - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ
ኢትዮጵያ ችግሮቿን ለመፍታተት "ለአፍሪካ ችግር አፍሪካዊ መፍትሄ" የሚለውን መርህ በተግባር እንደተጠቀመችበት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ተናገሩ።
“የአፍሪካ አህጉራዊ ነጻ የንግድ ቀጠና ትግበራን ማፋጠን” በሚል መሪ ሀሳብ የሚካሄደው 36ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ በአዲስ አበባ መካሄድ ጀምሯል።
በጉባኤው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን ጨምሮ የአፍሪካ አገራት መሪዎች እየተሳተፉ ይገኛሉ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በጉባኤው ላይ ባደረጉት ንግግር ኢትዮጵያ ባለፈው ዓመት ጦርነት ውስጥ እንደነበረች አስታውሰው፤ አሁን ግን በመንግስት እና በሕወሃት መካከል በደቡብ አፍሪካ በተደረሰው ስምምነት ሰላም መፍጠሯን ገልጸዋል፡፡
በዚህም ኢትዮጵያ በአፍሪካ ህብረት ያላሰለሰ ጥረት እና የአፍሪካን ችግር በአፍሪካዊ መፍትሔ መፍታት በሚለው መርህ ሳትከፋፈል መቆም መቻሏን ተናግረዋል፡፡
ኢትዮጵያ ችግሮቿን ለመፍታተት ለአፍሪካ ችግር አፍሪካዊ መፍትሄ የሚለውን መርህ በተግባር ተጠቅማ ማሳየቷንም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተናግረዋል፡፡
ኢትዮጵያ በሱዳን፣ ሶማሊያ እና ደቡብ ሱዳን እያካሄደችው ያለውን የሰላም ማስከበር ስራ አጠናክራ እንደቀጠለች የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ በኢትዮጵያ እና በኤርትራ መካከል ያለው ሰላምም በምሳሌነት የሚጠቀስ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top