የሩዋንዳ እና የሌሴቶ ፕሬዚዳንቶች በ36ኛው የአፍሪካ የመሪዎች ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ አዲስ አበባ ገቡ

1 Yr Ago
የሩዋንዳ እና የሌሴቶ ፕሬዚዳንቶች በ36ኛው የአፍሪካ የመሪዎች ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ አዲስ አበባ ገቡ

የሩዋንዳ ፕሬዚዳንት ፖል ካጋሜ እና የሌሴቶ ፕሬዚዳንት ሳም ማትኬኔ በ36ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ አዲስ አበባ ገብተዋል።

የሩዋንዳው ፕሬዚዳንት ፖል ካጋሜ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደረሱ የትራንስፖርት እና ሎጀስቲክስ ሚኒስትር ዶክተር ዓለሙ ስሜ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

የሌሴቶ ፕሬዚዳንት ሳም ማትኬኔ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ ደግሞ የባህል እና ስፖርት ሚኒስትር ቀጄላ መርዳሳ አቀባበል አድርገውላቸዋል። 

36ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ “የአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጣና ስምምነት ትግበራን ማፋጠን” በሚል መሪ ሃሳብ በመጪው ቅዳሜና እሁድ ይካሄዳል።

ከመሪዎቹ ጉባኤ ቀደም ብሎ የሚካሄደው 42ኛው የአፍሪካ ህብረት የስራ አስፈጻሚዎች ጉባኤ ከትናንት ጀምሮ እየተካሄደ መሆኑ ይታወቃል።

በ36ኛው የአፍሪካ የመሪዎች ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ በርካታ የአፍሪካ መሪዎች ወደ አዲስ አበባ በመግባት ላይ ሲሆኑ እስከ አሁንም የሴራሊዮን፣ የኮሞሮስ፣ የብሩንዲ፣ የታንዛኒያ፣ የአንጎላ ፕሬዚደንቶች እንዲሁም የኡጋንዳ እና የሊቢያ ምክትል ፕሬዚዳንቶችን ጨምሮ በርካታ የአፍሪካ አገራት መሪዎች መግባታቸው ይታወቃል።


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top