የኢንደስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን በበጀት ዓመቱ 330 ሚሊዮን ብር አተረፈ

1 Yr Ago
የኢንደስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን በበጀት ዓመቱ 330 ሚሊዮን ብር አተረፈ
የኢንደስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን በ2014 በጀት ዓመት 330 ሚሊዮን ብር ማግኘቱን የኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ሳንዶካን ደበበ አስታወቁ። አቶ ሳንዶካን ደበበ ይህን ያስታወቁት የኮርፖሬሽኑን የ2014 በጀት ዓመት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ለመገናኛ ብዙኃን ባቀረቡበት ወቅት ነው። ኮርፖሬሽኑ ባለፉት ዓመታት በኪሳራ ያለፈ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን ለአብነትም በ2013 በጀት ዓመት የ70 ሚሊዮን ብር ኪሳራ እንደደረሰበት አቶ ሳንዶካን ገልጸዋል። በ2014 በጀት ዓመት ኮርፖሬሽኑ ከሼድ ኪራይ፣ ከቢሮ አቅርቦት እና ሌሎች አገልግሎቶች 1.4 ቢሊዮን ብር ገቢ ለማግኘት ታቅዶ 1.2 ቢሊዮን ብር ገቢ መገኘቱን ተናግረዋል። በበጀት ዓመቱ ከኢንዱስትሪ ፓርኮች ኤክስፖርት 196 ሚሊዮን ዶላር መገኘቱን አቶ ሳንዶካን አስታውቀዋል። በበጀት ዓመቱ 57 ሺህ ዜጎች አዲስ የሥራ ዕድል ያገኙ ሲሆን በፖርኮቹ ውስጥ ያሉ ኩባንያዎች ለሀገር ውስጥ ገበያ ወይም ተኪ ምርት 161 ሚሊዮን ዶላር የሚገመት አስተዋጽኦ አድርገዋል ተብሏል። በበጀት ዓመቱ 13 የማምረቻ ሼዶች እና 6 ሔክታር የለማ መሬት ለአምራቾች መተላለፉን አቶ ሳንዶካን ገልጸው በአሁኑ ሰዓት ኮርፖሬሽኑ 526 ሔክታር የለማ መሬት እንዳለው ማመልከታቸውን ከኮርፔሬሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። ኮርፓሬሽኑ ተቋማዊ እና የቢዝነስ ለውጥ እያከናወነ መሆኑን የገለጹት አቶ ሳንዶካን የበጀት አስተዳደር እና የገቢ ምንጮችን ለማስፋት የተሠሩ ሥራዎች ባለፉት ሰባት ዓመታት ያልተገኘ ውጤት ዘንድሮ እንዲመጣ ማስቻሉን አስረድተዋል።
 
የቪዲዮ መረጃዎቻችንን ለማግኘት ትክክለኛውን የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
የተመረጡ አጫጭር የቪዲዮ መረጃዎቻችንን ለማግኘት ትክክለኛውን የቲክቶክ አካውንታችንን ይከተሉ

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top