በአማራ እና አፋር ክልል በጦርነቱ ጉዳት ለደረሰባቸው 6 የሆስፒታል ላብራቶሪዎች ድጋፍ ተደረገ

05/08/2022 01:19
በአማራ እና አፋር ክልል በጦርነቱ ጉዳት ለደረሰባቸው 6 የሆስፒታል ላብራቶሪዎች  ድጋፍ ተደረገ
በአማራ እና አፋር ክልል በጦርነት ጉዳት ለደረሰባቸው 6 የሆስፒታል ላብራቶሪዎች ከ9 ሚሊዮን ብር በላይ ዋጋ ያላቸው የላብራቶሪ የህክምና ቁሳቁሶች ድጋፍ ተደረገ። የኦሃዮ ዩኒቨርስቲ ግሎባል ዋን ሄልዝ ተቋም እና በአሜሪካ የበሽታ መቆጣጠሪያ እና መከላከያ ማዕከል (ሲዲሲ) በጋራ በመሆን ድጋፉን ለጤና ሚኒስቴር አስረክበዋል።
በሰሜኑ ጦርነት ጉዳት ለደረሰባቸው የአማራ እና አፋር ክልል የሆስፒታል ላብራቶሪዎች የሚደረገው ይህ ድጋፍ በሁለተኛ ዙር የቀረበ መሆኑንም በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኢምባሲ መረጃ ያመለክታል። የጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ፣ በሲዲሲ እየተደረገ ያለውን ድጋፍ አድንቀው የህክምና ቁሳቁሶቹ የላብራቶሪ ምርመራ አገልግሎት ለመስጠት፣ እንክብካቤና ህክምናን ለማሻሻል ትልቅ አስተዋፅኦ እንደሚኖራቸው ተናግረዋል። የቪዲዮ መረጃዎቻችንን ለማግኘት ትክክለኛውን የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
 
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
የተመረጡ አጫጭር የቪዲዮ መረጃዎቻችንን ለማግኘት ትክክለኛውን የቲክቶክ አካውንታችንን ይከተሉ
ግብረመልስ
Top