የሃይማኖት ቴሌቪዥን ጣቢያዎች እስከ ነሐሴ 13 እንዲመዘገቡ ባለሥልጣኑ ጥሪ አቀረበ

1 Yr Ago
የሃይማኖት ቴሌቪዥን ጣቢያዎች እስከ ነሐሴ 13 እንዲመዘገቡ ባለሥልጣኑ ጥሪ አቀረበ
የሃይማኖት ቴሌቪዥን ጣቢያዎች እስከ ነሐሴ 13 ቀን 2014 ዓ.ም ድረስ አመልክተው ፈቃድ እንዲወስዱ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ጥሪ አቀረበ። ጣቢያዎቹ https://www.eservices.gov.et/ በሚለው ፖርታል ውስጥ በመግባት ወይም በአካል በመቅረብ ማመልከት የሚችሉ መሆናቸውን ባለስልጣኑ ገልጿል።
የሃይማኖት ድርጅቶች አስተምህሮአቸውን በመገናኛ ብዙኃን ለማድረስ የብሮድካስት አገልግሎት ፈቃድ ማግኘት እንዳለባቸው የመገናኛ ብዙኃን አዋጅ ይደነግጋል። የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣንም በአዋጅ በተሰጠው ሥልጣን መሰረት ከሰኔ 27 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ የሃይማኖት የቴሌቪዥን ጣቢያዎችን በመመዝገብ ላይ መሆኑን ጠቅሷል። ስለዚህ ማንኛውም የሃይማኖት ቴሌቪዥን ጣቢያ በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ተመዝግቦ ፈቃድ እንዲወስድ ባለሥልጣኑ አሳስቧል።
 
የቪዲዮ መረጃዎቻችንን ለማግኘት ትክክለኛውን የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
የተመረጡ አጫጭር የቪዲዮ መረጃዎቻችንን ለማግኘት ትክክለኛውን የቲክቶክ አካውንታችንን ይከተሉ

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top