በአዲስ አበባ በትላንትናው ዕለት በጣለው ከባድ ዝናብ በንብረት እና በመሠረተ ልማት ላይ ጉዳት ደረሰ

01/08/2022 02:03
በአዲስ አበባ በትላንትናው ዕለት በጣለው ከባድ ዝናብ በንብረት እና በመሠረተ ልማት ላይ ጉዳት ደረሰ
በአዲስ አበባ ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 ልዩ ቦታው ፋና ወጊ በተባለ ቦታ በትላንትናው ዕለት (ሐምሌ 24 ቀን 2014 ዓ.ም) 9:00 ሰዓት ላይ በጣለው ከባድ ዝናብ በአካባቢው ነዋሪዎች ንብረት እና የኮብልስቶን ንጣፍ መንገድ እና የወንዝ ድጋፍ ግንባታ በመሳሰሉ መሠረት ልማቶች ላይ ጉዳት መድረሱን የከንቲባ ጽ/ቤት አስታወቀ።
በተጨማሪም በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ የወረዳ 9 እና የወረዳ 07 ነዋሪዎችን የሚያገናኝ ድልድይ ላይ ጉዳት መድረሱም ተገልጿል። በሌሎችም አከባቢዎች ለጎርፍ አደጋ ስጋት የሆኑ ቦታዎች ላይ ኅብረተሰቡ አስፈላጊውን ሁሉ ቅድመ ጥንቃቄ ያደርግ ዘንድ ጥሪ ቀርቧል።
ግብረመልስ
Top