"ጊዜው የህዳሴው ግድብ ለሶስቱ አገራት የሰላም፣የትብብር እና የአብሮ መኖር ተምሳሌትነቱን የምናሳይበት ነው"፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ

2 Yrs Ago
"ጊዜው የህዳሴው ግድብ ለሶስቱ አገራት የሰላም፣የትብብር እና የአብሮ መኖር ተምሳሌትነቱን የምናሳይበት ነው"፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጊዜው ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ለኢትዮጵያ፣ ግብፅ እና ሱዳን የሰላም፣ የትብብር እና የአብሮ መኖር ተምሳሌትነቱ የምናሳይበት ነው ነው ሲሉ ገልፀዋል።

ኢትዮጵያ በግብርና፣ በማምረቻው ዘርፍ እና በኢንዱስትሪ ላይ የተመሰረተ ዘመናዊ ኢኮኖሚ ለመገንባት ያላትን ህልም ለማሳካት የምትችለው የኤሌክትሪክ ኃይል አቅሟን ማሳደግ ስትችል ብቻ እንደሆነ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ጠቁመዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ዘርፍ በኩልም ጥራት ያለው ትምህርት፣ የጤና አገልግሎት እና ንፁህ የመጠጥ ውሃ ለዜጎች ለማቅረብ በቁርጠኝነት እንደሚሰራም አንስተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ዘርፍ በኩልም ጥራት ያለው ትምህርት፣ የጤና አገልግሎት እና ንፁህ የመጠጥ ውሃ ለዜጎች ለማቅረብ በቁርጠኝነት እንደሚሰራም አንስተዋል።

ኢትዮጵያ በመልከዓ ምድራዊ አቀማመጧም ሆነ ባላት የውኃ ሀብት ያላትን ከፍተኛ የኤሌክትሪክ ኃይል ፍላጎት ለማሟላት የውሃ ኃይሏን መጠቀም እንደሚገባትም ጠቅላይ ሚኒስትሩ  በማህበራዊ ትስስር  ገጻቸው ጠቁመዋል።

በአሁኑ ወቅት 53 በመቶ ወይንም ወደ 60 ሚሊዮን የሚሆኑ  ኢትዮጵያዊያን ዜጎች የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተጠቃሚ አለመሆናቸውን የጠቆሙት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፣ያለ ኤሌክትሪክ የትኛውም አገር ዘላቂ ልማት እና እድገት ሊያረጋግጥ አልቻለም ብለዋል።

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top