የሶማሊያ መሪዎች ወቅታዊ አለመግባባቶችን በሰላማዊ ውይይት እንዲፈቱ የአፍሪካ ህብረት አሳሰበ

2 Yrs Ago
የሶማሊያ መሪዎች ወቅታዊ አለመግባባቶችን በሰላማዊ ውይይት እንዲፈቱ የአፍሪካ ህብረት አሳሰበ

የሶማሊያ መሪዎች ወቅታዊ አለመግባባቶችን በሰላማዊ ውይይት እንዲፈቱ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ ማህመት አሳሰቡ።

የኮሚሽኑ ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ ማህመት በወቅታዊ የሶማሊያ መሪዎች ፖለቲካዊ አለመግባባት ዙሪያ መግለጫ አውጥተዋል።

ሊቀመንበሩ በመግለጫቸው የአፍሪካ ህብረት የሶማሊያን ፖለቲካዊ አለመረጋጋት በትኩረት እየተከታተለው ነው ብለዋል።

አክለውም የሶማሊያው ፕሬዚዳንት ሞሃመድ አብዱላሂ ፋርማጆ እና ጠቅላይ ሚኒስትር ሞሃመድ ሁሴን ሮብሌ በመካከላቸው ያለውን አለመግባባት በውይይት እንዲፈቱ አሳስበዋል ሲል የዘገበው ኢዜአ ነው።

መሪዎቹ ሀገሪቱን የባሰ አደጋ ላይ ከሚጥል እንቅስቃሴ እንዲቆጠቡም ነው ሙሳ ፋኪ ያስጠነቀቁት።

የአፍሪካ ህብረት በሶማሊያ ያለው የሰላም እጦት እና አለመረጋጋት እንዲፈታ በላቀ ሁኔታ እንደሚሰራም አረጋግጠዋል።


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top