አንዳንድ ሀገራት የተመድ የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤትን ለራሳቸው የፖለቲካ አጀንዳ ማስፈፀሚያ አድርገው መጠቀማቸው እንዳሳዘናት ኢትዮጵያ ገለፀች

2 Yrs Ago
አንዳንድ ሀገራት የተመድ የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤትን ለራሳቸው የፖለቲካ አጀንዳ ማስፈፀሚያ አድርገው መጠቀማቸው እንዳሳዘናት ኢትዮጵያ ገለፀች

የተመድ የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤትን አንዳንድ ሀገራት ኢትዮጵያን በተመለከተ የራሳቸውን የፖለቲካ አጀንዳ ለማራመድ እየተጠቀሙበት መሆኑን መንግስት አስታወቀ።

በሁኔታው ማዘኑን ያስታወቀው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በመግለጫው፣ የተመድ የሰብዓዊ መብት ከፍተኛ ኮሚሽንና የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ተፈፅመዋል በተባሉ ጥሰቶች ላይ በጋራ ጥናትና ምርመራ አድርገው የጋራ ሪፖርት አውጥተው እያለ አንዳንድ አገራት በተቃራኒ የሚያራምዱት አቋም ተቀባይት የለውም ብሏል።

ይልቁንም መንግስት የጋራ ሪፖርት ውጤቱን ተቀብሎ ከፍተኛ የሚኒስትሮች ግብረሃይል አቋቁሞ ምክረ ሀሳቦችን ለመተግበር እየሰራ መሆኑን ጠቁሟል።

ይህ በሆነበት ሁኔታ አንዳንድ የተመድ የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት አባል ሀገራት ኢትዮጵያን በተመለከተ የራሳቸውን የፖለቲካ አጀንዳ በመያዝ እና ይህንንም አጀንዳቸውን በምክር ቤቱ በኩል ለመፈፀም ምክር ቤቱ በጉዳዩ ላይ ልዩ ስብሰባ እንዲያደርግ በመጥራት ላይ መሆናቸውን አንስቷል።

በአንጻሩ ምክር ቤቱ አሸባሪው የህወሓት ቡድን በአማራ እና አፋር ክልሎች የፈፀማቸውን እጅግ ዘግናኝ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን አጀንዳ አድርጎ ሊወያይና ሊያወግዘው በተገባ ነበር ብሏል መግለጫው።

የምክር ቤቱ አባል ሀገራትም ይህንን የተወሰኑ ሀገራትን የፖለቲካ ፍላጎት ያነገበን ልዩ ስብሰባ እና ውጤቱን በጥብቅ እንዲቃወሙ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በመግለጫው ጠይቋል።

የቪዲዮ መረጃዎቻችንን ለማግኘት ትክክለኛውን የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
https://www.youtube.com/c/EBCworld/
የመዝናኛ ቻናላችን የቪዲዮ መረጃዎችን ለማግኘት የዩቲዩብ የመዝናኛ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
https://www.youtube.com/channel/UCp9pS23Vw1n8WpcpZBDJNmA
በምስል የሚገኙ መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የኢንስታግራም ገፃችንን ይከተሉ
https://www.instagram.com/ebcnews1/
አጫጭርና ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት የትዊተር ገፃችንን ይከተሉ
https://twitter.com/ebczena
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
https://t.me/EBCNEWSNOW


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top