ፕሬዝደንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ አነስተኛ ገቢ ላላቸው የእስልምና እምነት ተከታዮች ስጦታ አበረከቱ

17/05/2020 12:33
ፕሬዝደንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ አነስተኛ ገቢ ላላቸው የእስልምና እምነት ተከታዮች ስጦታ አበረከቱፕሬዝደንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ ዛሬ ረፋዱን በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ልዩ ስሙ መሳለሚያ እህል በረንዳ አካበቢ በመገኘት አነስተኛ ገቢ ያላቸውን የእስልምና እምነት ተከታዮችን ጠይቀዋል፡፡

ከእነርሱም መካከል የበርካታ ቤተሰብ ኃላፊነት ያለባቸውና ኑሮአቸውን በብዙ ችግር የሚመሩ እማወራዎችን አነጋግረዋል::

የበግ፤ሩዝ፤ዱቄት፤ዘይት እና ቴምር ስጦታም በማበርከት "እንኳን አደረሳችሁ ብለዋል፡፡

በችግር ጊዜ የመረዳዳት እና የመደጋገፍን አስፈላጊነት ያሳሰቡ ሲሆን ''ለአንድ ወቅት ብቻ ሳይሆን ጠንካራ ባህላችን እናድርገው" ብለዋል፡፡

ወቅታዊውን የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ለመከላከልም መንግሥት የሚያወጣቸው መመርያዎችን ማክበር እንደማያስፈልግና የህክምና ባለሙያዎችን ምክር በተጠናከረ ሁኔታ መተግበር እንደሚገባ መናገራቸውን ከፕሬዝዳንት ጽ/ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

ግብረመልስ
Top