የሃገር መከላከያ ሰራዊት በጎፋ ዞን በደረሰው አደጋ ለተጎዱ ወገኖች የ 6.3 ሚሊየን ብር የአይነት ድጋፍ አደረገ

4 Mons Ago 516
የሃገር መከላከያ ሰራዊት በጎፋ ዞን በደረሰው አደጋ ለተጎዱ ወገኖች የ 6.3 ሚሊየን ብር የአይነት ድጋፍ አደረገ

የሃገር መከላከያ ሰራዊት በጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ በኬንቾ ቀበሌ በደረሰው የመሬት መንሸራተት አደጋ የተጎዱ ወገኖችን ለመደገፍ የ 6.3 ሚሊየን ብር የአይነት ድጋፍ አድርጓል።

ድጋፉን ያስረከቡት የመከላከያ ሰራዊት የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ኮሎኔል ጌትነት አዳነ፤ የሰራዊቱ አመራር እና አባላት በአደጋው ህይወታቸውን ባጡት ወገኖች ከልብ አዝኗል ብለዋል።

ሰራዊቱ ሀገር ሰው ሰራሽም ሆነ የተፈጥሮ አደጋ ባጋጠማት ጊዜ ፈጥኖ መገኘት ተልዕኮው በመሆኑ በቀጣይም ከተጎዱት ጎን እንቆማለን ሲሉ ኮሎኔል ጌትነት አዳነ ገልጸዋል። 

ድጋፉ የተለያዩ የምግብ ግብዓቶች እና አልባሳትን ያካተተ ሲሆን፤ በአጠቃላይ ከ6 ነጥብ 3 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት ነው።

በአስረሳው ወገሼ


Feedback
Top