Search

የትግራይ ክልል ባለአደራ አመራር ከደቡብ ምስራቅ ዞን አመራሮች ጋር እየተወያየ ነው

ዓርብ ኅዳር 04, 2019 211

የትግራይ ክልል ባለአደራ አመራር ከደቡብ ምስራቅ ዞን አመራሮች ጋር እየተወያየ ይገኛል።

በባለአደራ አስተዳደሩ የኢኮኖሚና መልሶ ግንባታ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ቴዎድሮስ አረጋይ (ዶ/ር) በውይይቱ መክፈቻ ላይ ባደረጉት ንግግር፣ ሕዝብን ያማከለ ሥራ በመሠራቱ በክልሉ ተጨባጭ ለውጦች መምጣታቸውን ተናግረዋል።

በክልሉ የሚታዩ ችግሮችን በሂደት የመፍታት ሥራ በትኩረት እየተከናወነ መሆኑን ገልጸው፣ የነዳጅ ችግርን በፍጥነት ለመቅረፍ እየተሠራ መሆኑንም አመላክተዋል።

በውይይቱ በዞኑ የሚገኙ የስድስቱ ወረዳ አመራሮች የተገኙ ሲሆን፣ በባለአደራ አስተዳደሩ የፖለቲካና ሕዝብ አደረጃጀት ዋና ሥራ አስፈፃሚ ረዳኢ ሀለፎም በለውጡ የመጡ ውጤቶች እና በቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ ጥናታዊ ጽሑፍ አቅርበው ውይይት እየተደረገባቸው ነው።

በጥናቱ 11 የተለዩ ዋና የትኩረት አቅጣጫዎች የቀረቡ ሲሆን፣ በእነዚህ ላይ እስከታችኛው መዋቅር በትኩረት እንደሚሠራባቸው ተመላክቷል።

 

በአስማረ ብርሃኑ

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: