Search

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የዜጎችን የኤሌክትሪክ ኃይል ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚያደርገውን ጥረት አጠናክሮ ይቀጥላል

ዓርብ ኅዳር 04, 2019 206

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በ2019 በጀት ዓመት ጥቅምት ወር ውስጥ የኤሌክትሪክ ኃይል ተዳራሽነትን ለማስፋፋት ባከናወናቸው ተግባራት 16 ከተሞችንና መንደሮችን የኤሌክትሪክ ኃይል ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን ገለጸ።

አገልግሎቱ ባከናወነው የኃይል መስመር ዝርጋታ ሥራ በዋናው መረብ 15 ከተሞች እንዲሁም በኦፍ ግሪድ  አማራጭ 1 ከተማ በድምሩ 16 ከተሞችና መንደሮች የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተጠቃሚ ማድረጉን ነው የገለጸው።

 

በዚህም በዋናው መረብ 79 ነጥብ 05 ኪሎ ሜትር እና ከመረብ ውጪ 0 ነጥብ 36 ኪሎ ሜትር በድምሩ 79 ነጥብ 41 ኪሎ ሜትር የመካከለኛ መስመር ዝርጋታ ማከናወኑን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የኮሙኒኬሽን ሥራ አስፈጻሚ አንዋር አብራር ለኢቢሲ ዶትስትሪም አስታውቀዋል።

በተጨማሪም በዋናው መረብ 189 ነጥብ 35 ኪሎ ሜትር እና ከመረብ ውጪ 3 ነጥብ 95 ኪሎ ሜትር በድምሩ 193 ነጥብ 3 ኪሎ ሜትር የዝቅተኛ መስመር ዝርጋታ ሥራ መከናወኑን ገልጸዋል። 

ከትራንስፎርመር ተከላ ጋር በተያያዘ ለአገልግሎት ማሻሻያ እና ማስፋፊያ በዋናው መረብ 44 እና ከመረብ ውጪ 1 በድምሩ 45 ትራንስፎርመሮች ተተክለው አገልግሎት መስጠት መጀመራቸውን ጠቁመዋል። 

በአጠቃላይ በእነዚህ ከተሞች አዳዲስ ደንበኞችን የኃይል ተጠቃሚ ለማድረግ በዋናው መረብ 4 ነጥብ 329 እና ከመረብ ውጪ 774 በድምሩ 5 ሺህ 103 የኤሌክትሪክ ቆጣሪዎች ተገጥመው ወደ ሥራ ገብተዋል ብለዋል።

 

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የዜጎችን የኤሌክትሪክ ኃይል ተጠቃሚነት ለማረጋገጥና የኢኮኖሚ እንቅስቃሴውን ለመደገፍ የሚያደርገውን የመሰረተ ልማት ማስፋፋት አጠናክሮ እንደሚቀጥልም አመላክተዋል።

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: