Search

የኦቢኤን የቀድሞ ዋና ዳይሬክተር አቶ ግዛቸው ገቢሳ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

ዓርብ ኅዳር 04, 2019 215

የኦሮሚያ ብሮድካስቲንግ ኔትወርክ (ኦቢኤን) የቀድሞ ዋና ዳይሬክተር አቶ ግዛቸው ገቢሳ በሕመም ምክንያት ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።

አቶ ግዛቸው በኦሮሚያ ራዲዮ እና ቴሌቪዥን ድርጅት ውስጥ ከሪፖርተር እስከ ዋና አዘጋጅነት፣ በኦሮሚያ ኮሙኒኬሽን ቢሮ እና በብልጽግና ፓርቲ የኦሮሚያ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የሕዝብ ግንኙነት እና የሕዝብ አስተያየት ዘርፍ ኃላፊ በመሆን አገልግለዋል።

አቶ ግዛቸው ገቢሳ ከሚያዚያ 2014 ዓ.ም ጀምሮ የኦቢኤን ዋና ዳይሬክተር በመሆን ያገለገሉ ሲሆን፣ የሚዲያ ኢንዱስትሪውን በማሳደግ ረገድም ከፍተኛ አስተዋጽኦ አበርክተዋል።

 

ከጥቂት ዓመታት በፊት ታመው በሕክምና ላይ የቆዩ ሲሆን፣ ኅዳር 3 ቀን 2019 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸውን ኦቢኤን ዘግቧል።

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: