Search

በመቐለ ከተማ ኮሪደር ልማት ፕሮጀክት ዙሪያ ከሃይማኖት መሪዎችና ሀገር ሽማግሌዎች ጋር ውይይት ተካሄደ

ዓርብ ኅዳር 04, 2019 167

በትግራይ ክልል መቐለ ከተማ የሃይማኖት መሪዎች እና የሀገር ሽማግሌዎች በተገኙበት በኮሪደር ልማት ዙሪያ ውይይት ተካሂዷል።

በውይይቱ በትግራይ ክልል ባለአደራ አስተዳደር የመቐለ ከተማ ከንቲባ ሺሻይ አማረ (ዶ/ር) እና የከተማዋ ኮሪደር ልማት ፕሮጀክት ዋና ሥራ አስኪያጅ ኢንጂነር ፀጋዘኣብ ኪዳኑ ተገኝተው ማብራሪያና ገለፃ አድርገዋል።

ፕሮጀክቱ እንደ መነሻ ፓይለት ፕሮጀክት መጀመሪያ ላይ ከመኖሪያ አካባቢው ብዙም ያልተቀራረበና የመኖሪያ ቤቶችን እና ተቋማትን በማይጎዳ መልኩ ለመሥራት ቅድሚያ የተሰጠበት መሆኑ ተጠቅሷል።

በተጨማሪም ለወጣቶች የሥራ ዕድል ተጠቃሚነት ብሎም በየደረጃው ያለ አመራር ጠንካራ የሥራ ባህል ለማዳበር የማያግዝ ቅድሚያ ትኩረት እንደተደረገበት ተገልጿል።

ማኅበረሰቡ የልማት ኮሪደሩ በፍጥነት እንዲጀመር ያለው ፍላጎት መነሻ በማድረግ የክፍለ ከተሞች አመራሮችም በቁርጠኝነት እንደሚያግዙ ሐሳብ አቅርበዋል።

ውይይቱ ከንግድ ማኅበረሰብ፣ ከአካዳሚክ ባለሙያዎች እና ከተለያዩ የማኅበረሰቡ ክፍል ተወካዮች ጋርም እንደሚቀጥል ተመላክቷል።

 

በአስማረ ብርሃኑ

 

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: