Search

በመቐለ ከተማ 80 በመቶ የፖሊስ አባላት ወደ መደበኛ ሥራቸው ተመልሰዋል

ሓሙስ ኅዳር 03, 2019 216

የመቐለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ከከተማዋ ፖሊስ አባላት ጋር በቀጣይ የሥራ አቅጣጫዎች ዙሪያ ላይ ውይይት እያደረገ ይገኛል።

የመቐለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ወንጀል መከላከል ኃላፊ ም/ኮማንደር ሙሉ አብረሃ በዚሁ ወቅት እንደገለጹት፣ አሁን ላይ በመቐሌ ከተማ 80 በመቶ የሚሆነው የፖሊስ አባል ወደ መደበኛ ሥራቸው  ተመልሰዋል።

የውይይት መድረኩ ከሕብረተሰቡ ጋር በመቀናጀት ወንጀልን የመከላከል አቅምን ለማጠናከር ያለመ መሆኑን ገልጸው፣ የፖሊስ አባላት ከሕብረተሰቡ ጋር በመቀናጀት ወንጀልን ለመከላከልና የሕብረተሰቡን ደኅንነት ለማስጠበቅ ያደረገውን ቁርጠኝነት አድንቀዋል።

በመድረኩ የመቐለ ከተማ ባለአደራ አስተዳደር ከንቲባ ሺሻይ አማረን (ዶ/ር) ጨምሮ ሌሎች የባለአደራ አስተዳደሩ አመራሮች ተገኝተዋል።

 

በአስማረ ብርሃኑ

 

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: