Search

መሬ ሆ… ጉዞ ወደ መልካ ፊንፊኔ!

ቅዳሜ መስከረም 23, 2019 79

የኢሬቻ ሆረ ፊንፊኔ ‘የኢሬፈና’ /ምስጋና የማቅረብ/ ሥነ-ሥርዓት እየተካሄደ ነው።

አባ ገዳዎች እና ሃደ ሲንቄዎች፣ ቄሮ እና ቀሬዎች ለምለም ሣር እና አደይ አበባ ይዘው “መሬ ሆ…!” እያሉ በታላቅ እልልታ እና ምስጋና ወደ መልካ አቅንተዋል።

“ጉዲቻ መርጋ ቶሌ

ሆያ  ያ መሬ  ሆ.....

ጉራቻ ገራን ቡሌ

ሆ ያ መሬ ሆ

መሬ ሆ ...

ኡርጋን ኬ ፎሊ ኬ

ሆ ያ  መሬ ሆ.....

መሬ ሆ … እያሉ ጭጋጉ መገፈፉን፣ ፈጣሪያቸው ምሕረት ማድረጉን ከዘመን ዘመን ማሸጋገሩን እየገለጹም ይገኛሉ።

‘መሬ ሆ’ የሚለው አገላለጽ የደስታ፣ የምስጋና እና የአንድነት ስሜትን ለመግለጽ ይሰማል።

ስለዚህ ሰዎች ‘መሬ ሆ!’ ብለው በጋራ ወደ ሆራ ሲወርዱ በበዓሉ ላይ ያላቸውን ደስታ እና ምስጋና በጋራ ይገልጻሉ።”

ያለፈውን ዓመት በሰላም አሳልፈህ ዘንድሮ ያደረስከን ፈጣሪ ምስጋና ይገባሀል እያሉ ኢሬቻን ያከብራሉ።

#ትልቅ_ሀገር! #ትልቅ_ሕዝብ! #ታላቅ_ርዕይ!

 

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: