Search

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የ2019 በጀት 85 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር በላይ ሆኖ ፀደቀ

ቅዳሜ ሐምሌ 18, 2018 96

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት እያካሄደ በሚገኘው 6ኛው ዙር 5 የሥራ ዓመት 7 መደበኛ ጉባኤው የክልሉ 2019 በጀት 85 ቢሊዮን 774 ሚሊዮን 12 ሺህ 25 ብር ሆኖ እንዲፀድቅ በሙሉ ድምፅ ወስኗል።

የበጀት ድልድልም ለክልል ማዕከል መሥሪያ ቤቶች መደበኛ እና የካፒታል - 7ቢሊዮን 527ሚሊዮን 155 ሺህ 180 ብር፣ ለዞኖች እና ለከተማ አስተዳደሮች ጥቅል በጀት -70 ቢሊዮን 592 ሚሊዮን 656 ሺህ 845 ብር፣ ለክልላዊ ፕሮግራም - 6 ቢሊዮን 500 ሚሊዮን ብር፣ ለዘላቂ ልማት ግቦች ማስፈጸሚያ - 984 ሚሊዮን 200 ሺህ ብር፣ ለመጠባበቂያ - 170 ሚሊዮን ብር፤ ጠቅላላ ድምር - 85 ቢሊዮን 774 ሚሊዮን 12 ሺህ 25 ብር ሆኖ በሙሉ ድምፅ ፀድቋል።

ከበጀቱ 20 በመቶ ለክልል ማዕከላት እንዲሁም 80 በመቶው ለዞን አስተዳደር እርከኖች የሚውል መሆኑ ተገልጿል።

በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የክልሉ የፋይናንስ ቢሮ ኃላፊ አቶ ተፈሪ አባቴ በጀት ድልድልም ፈጣን እና ዘላቂ ዕድገታችንን በማስቀጠል የዜጎችን የኑሮ ሁኔታ ለማሻሻል ታሳቢ ተደርጎ መዘጋጀቱን ገልጸዋል።

በትዕግሥቱ ቡቼ

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: