የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤ በአርባምንጭ ከተማ እየተካሄደ ነው።
በምክር ቤቱ በጉባኤ ሁለተኛ ቀን ውሎ ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ የክልሉን የ2019 በጀት ዓመት ጠቋሚ ዕቅድ ለምክር ቤቱ አቅርበዋል።
በግብርና ፣ በቱሪዝም ፣ በሥራ ዕድል ፈጠራ እና ማሕበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮችን አቀናጅቶ በመምራት የተሻለ አፈፃፀም ለማስመዝገብ እንድሚስራ ጠቁመዋል።
የልማት ሥራዎች ለወጣቶች የሥራ አማራጭ እንዲሆኑ የማድረግ ሥራ የዓመቱ ትኩረት መሆኑንም ለምክር ቤቱ አባላት ተናግረዋል።
እንደ ሀገር የተጀመረው አዲሱ ጀምሮ የመጨረስ ባህልን በከልሉ ለማስቀጠል እንደሚሰራም ርዕሰ መስተዳድሩ ተናገረዋል።
ፕሮጀክቶች በተቀመጠላቸው ጊዜ በጥራት እንዲጠናቀቁ ትኩረት ይሰጣል ያሉት ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ በዚህም ከምርጫ ማግስት ጠንካራ መንግሥት ብለን የጀመርነው ጉዞ እናሳካለን ብለዋል።
ዘላቂ ሠላምን ለማስፈን ሕብረተሰቡ የተሳተፈበት የጋራ ዕቅድ በማዘጋጀት ሁሉም በባለቤትነት እንዲሠራ እየተደረገ ስለመሆኑም ለምክር ቤቱ አባላት ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡
ከተሞችን ለነዋሪዎች ምቹ የማድረግ ሥራዎችን በማስቀጥል የወንዝ ዳርቻ ልማት ሕብረተሰቡን በማሳተፍ ትኩረት ይሰጥባቸዋል ።
የበጎ ፈቃድ ተግባራት የሁልጊዜ ባህል ሊሆን እንደሚገባ የጠቆሙት ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ በክረምቱ ወራት ወጣቶችን በማሳተፍ እገዛ ለሚያስፈልጉ ወገኖቻችን ልንደርስ ይገባል ብለዋል።
ምክር ቤቱ የ2019 ዓ.ም በጀትን ማጽደቅ ጨምሮ የተለያዩ ውሳኔዎችን ያሳልፋሉ ተብሎ ይጠበቃል።
በትዕግስቱ ቡቼ
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: