6ኛው የሄንግይሹይ ሐይቅ ዳርቻ ዓለም አቀፍ የማራቶን ውድድር ነገ ይካሄዳል

መስከረም 19፣2010

ነገ በሚካሄደው 6ኛው የሄንግሹይ ሐይቅ ዳርቻ ዓለም አቀፍ የማራቶን ውድድር ኢትዮጵያዊው ቦንሳ ዲዳ ትልቅ ግምት ተሰጥቶታል።

በሙሞባይ ማራቶን 2፡09፡47 ሰከንድ በመግባት የራሱን ምርጥ ሰዓት ያስመዘገበው የ22 ዓመቱ ቦንሳ ዲዳ በ2014 በሌላኛው ኢትዮጵያዊ ማርቆስ ገነቴ የተያዘውን የውድድሩን ሪከርድ 2፡07፡38 ሰአት ያሻሽላል ተብሎም ይጠበቃል፡፡

ረጋሳ ምንዳዬም በውድድሩ የሚጠበቅ ሌላኛው ኢትዮጵያዊ አትሌት ነው፡፡

ረጋሳ ቻይና ውስጥ ከተካሄዱ የማራቶን ውድድሮች አምስት ጊዜ አሸንፏል፡፡

በሴቶች ትዕግስት ማሙዬ እና ትዝታ ተሬቻ ተጠባቂዎች ናቸው፡፡በሁለቱም ፆታዎቸ የኢትዮጵያዊያን ተፎካካሪዎች ይሆናሉ ተብለው የአሸናፊነት ግምት የተሰጣቸው ኬኒያዊያን አትሌቶች ናቸው፡፡

Average (0 Votes)

ተያያዥ ዜናዎች ተያያዥ ዜናዎች