46ኛው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና የፊታችን ማክሰኞ በአዲስ አበባ ይጀመራል

ግንቦት 03፣ 2009

ለስድስት ቀናት የሚቆየው 46ኛው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና የፊታችን ማክሰኞ በአዲስ አበባ ስታዲዮም ይጀመራል።

በአገር አቀፍ ደረጃ የሚካሄደው ይኸው ውድድር ተተኪ አትሌቶችን ለማፍራት ያለመ መሆኑን  የኢትዮጵያ  አትሌቲክስ ፌደሬሽን  አስታውቋል።

ከግንቦት 8 – 13/2009 ዓ. ም.  በሚካሄደው  በዚሁ  የውድድር መድረክ ከክልሎች፣ ከከተማ አስተዳድሮች፣ ከክለቦችና ከማሠልጠኛ ማዕከላት የሚውጣጡ 1300 አትሌቶች ተሳታፊዎች ይሆናሉ።

ታዋቂ  አትሌቶች የውድድሩ ተካፋይ እንደሚሆኑም ፌድሬሽኑ አመለክቷል።

በሻምፒዮናው 42 የውድድር ዓይነቶች ላይ አትሌቶችየሚሳተፉ ይሆናል። 

 በውድድሩ  የተሻለ  ብቃት ያሳዩ አትሌቶች ለ16ኛው የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያን ወክለው እንዲወዳደሩ የምመረጡበት መሆኑንም ፌድሬሽኑ አመልክቷል።

ምንጭ ፥ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌደሬሽን

 

 

Average (0 Votes)

ተያያዥ ዜናዎች ተያያዥ ዜናዎች