ዩዚያን ቦልት በቤጂንግ ኦሊምፒክ በ4x100 ሜትር የዱላ ቅብብል ያገኘውን ወርቅ ሊነጠቅ ነው

ጥር 18፣2009

ዩዚያን ቦልት በቤጂንግ ኦሊምፒክ በ4x100 ሜትር የዱላ ቅብብል ያገኘውን ወርቅ ሊነጠቅ ነው።

በፈረንጆቹ 2008 በተካሄደው የቤጂንግ ኦሊምፒክ በ4x100 ሜትር የዱላ ቅብብል ውድድር ጃማይካ የወርቅ ሜዳሊያ ማገኘቷ ይታወሳል፡፡

ይሁንና ከተወዳዳሪዎቹ መካከል ኔስታ ካርተር የተባለው ሯጭ የተከለከለ አበረታች መድሃኒት መጠቀሙ በምርመራ በመረጋገጡ እሱና የቡድኑ አጋሮች ያገኙትን የወርቅ ሜዳሊያውን እንዲመልሱ ይደረጋል ተብሏል፡፡

ኔስታ ካርተር በቤጂንግ ኦሊምፒክ በ4x100 ሜትር የዱላ ቅብብል ሀገሩ የወርቅ ሜዳሊያውን ስታገኝ እሱና የቡድኑ አባላት በ37.10 ሰከንድ የአለም ክብረ ወሰንን በማሻሻል ነበር ያሸነፉት፡፡

ኔስታ ካርተር በፈረንጆቹ 2008 እና 2012 100ሜ፤ 200ሜ እና በ4x100 ሜትር የዱላ ቅብብል ውድድሮች የወርቅ ሜዳሊያ አግኝቶ ነበር፡፡

የጃማይካ አትሌቲክ ፌደሬሽነ ሃላፊ ዶ/ር ዋረን ብሌክ እንደተናገሩት ከሆነ ሁሉም የርቀቱ አሸናፊዎች አባላት በጅምላ ሊቀጡ አይገባም፡፡

የካርተር ጠበቃ በበኩሉ አትሌቱ ለአለም አቀፉ የስፖርት ገላጋይ ፍርድ ቤት ይግባኝ እንደሚጠይቅ አስታውቋል፡፡

ምንጭ ቢቢሲ

 

Average (0 Votes)

ተያያዥ ዜናዎች ተያያዥ ዜናዎች