ማንችስተር ዩናይትድ ኤቨርተንን 4 ለ0 በሆነ ሰፊ ውጤት አሸነፈ

መስከረም 07፣2010

የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 5ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ትናንትና እና ዛሬ ተካሂደዋል።

በሜዳው ኦልትራፎድ ኤቨርተንን ያስተናገደው ማንችስተር ዩናይትድ 4 ለ0 በሆነ ሰፊ ውጤት አሸንፏል፡፡

የቀድሞ ክለቡን የገጠመው ዋይኒ ሩኒ በሽንፈት ጨዋታውን አጠናቋል፡፡ በጨዋታው መጀመሪያ አንቶዮ ቫለንሺያ ባስቆጠራት ጎል ዩናይትድ የመጀመሪያው አጋማሽ 1 ለ0 ማጠናቀቅ ችሏል፡፡

ከእረፍት መልስ ተጨማሪ ጎል ማስቆጠር የተሳነው ዩናይትድ በጨዋታው መጠናቀቂያ ላይ በ83ኛው በሚኪታሪያ ሁለተኛውን  ሉካኩ በ89 ደቂቃ ተቀይሮ የገባው ማርሻል በፍጹም ቅጣት ምት በ92 ዲቂቃ ባስቆጠሩት ጎል 4 ለ0 በሆነ ውጤት ተጠናቋል፡፡

ዛሬ በተደረገ  ሌላ  ጨዋታ   ቸልሲ ከአርሰናል ያለምንም ጎል0ለ0 በሆነ የአቻ ውጤት ተጠናቋል። አርሰናል ከስድስት ዓመት በኃላ የመጀመሪያ ነጥብ በቼልሲ አግኝቷል ፡፡ በጨዋታ መጠናቀቂያ ላይ ዲቪድ ሉዊዝ በቀይ ካርድ ከሜዳ ተሰናብቷ፡፡ 

ትላንት በተደገው ጨዋታ  ማንችስተር ሲቲ ዋትፎርድን 6 ለ0 በሆነ ውጤት ማሸነፉ ይታወሳል፡፡ ለሲቲ  አጉዌሮ ሃትሪክ ሲሰራ ገብርኤል ጂሰን  ኦታሜንዲ እና ስተርሊግ የሲቲ ጎል ያስቆጠሩ ናቸው፡፡ሌሎች ትላንት የተደረጉ ጨዋታዎች  ሊቨርፑል1-1 ከበርንሌይ፣ ኒው ካስትል 21 ከስቶክ ሲቲ፣ ዌስት ብሮም0 ከዌስት ሃም0 ለ0 ተለያይትተዋል፡፡

 

Average (0 Votes)

ተያያዥ ዜናዎች ተያያዥ ዜናዎች