ብሄራዊ ቡድኑ በወዳጅነት ጨዋታው 4ለ0 ተሸነፈ

መስከረም 30፤2010

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ትናንት ምሽት ራባት ላይ ከሞሮኮ ብሄራዊ ቡድን ጋር ባደረገው የወዳጅነት ጨዋታ 4ለ0 ተሸንፏል፡፡

የሞሮኮ እግር ኳስ ፌድሬሽን ለኢትዮጵያ አቻው ባቀረበው የወዳጅነት ጨዋታ ግብዣ መሰረት ማክሰኞ ይደረጋል የተባለው ጨዋታ ባልታወቀ ምክንያት ትናንት ተካሂዷል፡፡

ወደ ጋቦሮኒ አቅንቶ በቦትስዋና የተሸነፈው ብሄራዊ ቡድኑ ከሰኔ ወር ጀምሮ በሁሉም ውድድሮች ካደረጋቸው ጨዋታዎች 8 ጨዋታዎች በአሰልጣኝ አሸናፊ በቀለ እየተመራ ማሸነፍ የቻለው 1 ጨዋታ ማለትም ከጅቡቲ ጋር ያደረገውን ብቻ ነው፡፡

ሞሮኮ እና ዋሊያዎቹ ባደረጉት ጨዋታ የመጀመሪያው አጋማሽ ሞሮኮ 3-0 መምራት ስትችል ከእረፍት መልስ አንድ ግብ አክላ 4ለ0 በሆነ ሰፊ ውጤት ማሸነፍ ችላለች፡፡

ብሄራዊ ቡድኑ ግጥሚያውን ያደረገው ሞሮኮ ለቻን የአፍሪካ ዋንጫ ውድድር ካዘጋጀችው ብሄራዊ ቡድን ጋር መሆኑ ተነግሯል፡፡

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን በተደጋጋሚ በሚያደርጋቸው ጨዋታዎች ሽንፈት ማስተናገዱን ቀጥሏል፡፡ ቡድኑ በሐምሌ ወር ጅቡቲን በቻን ማጣሪያ 5-1 ያሸነፈበት ውጤት ብቻ ነው ድል ሆኖ የተመዘገበው፡፡  ከሰባት ጨዋታዎች በአራቱ ሲሸነፍ በሶስቱ ደግሞ አቻ ተለያይቷል፡፡

በዳንኤል ንጉሴ

Average (0 Votes)

ተያያዥ ዜናዎች ተያያዥ ዜናዎች