የ31ኛው አፍሪካ ዋንጫ አሸናፊ ካሜሮን በፊፋ ወርሃዊ የአገራት ደረጃ 29 ደረጃዎችን አሻሻለች

የካቲት 03፣2009

የ31ኛው አፍሪካ ዋንጫ አሸናፊ ካሜሮን በፊፋ ወርሃዊ የአገራት ደረጃ 29 ደረጃዎችን አሻሻለች።  

ፊፋ ባወጣው የጥር ወር የአገራት ደረጃ 29 ደረጃዎችን በማሻሻል ከአለም የ23ኛ  ደረጃን አግኝታለች።ከአፍሪካ ደግሞ  ወደ ሶሽተኛነት ከፍ ብላለች።

ከካሜሮን ጋር  ለዋንጫ የደረሰችው ግብፅ ደግሞ ከአለም 21ኛ ደረጃን ስትይዝ፣ ከአፍሪካ ደግሞ በአንደኛ  ደረጃነት ተቀምጣለች።

ኢትዮጵያ ደግሞ 9 ደረጃዎችን በማሻሻል 103ኛ ደረጃን አግኝታለች።የአፍሪካ  ደረጃዋ ደግሞ  30ኛ ላይ ሆኗል።

ምንጭ፥ ፊፋ

Average (0 Votes)

ተያያዥ ዜናዎች ተያያዥ ዜናዎች