ከ30 በላይ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በአለም አቀፍ ውድድሮች ድል ቀንቷቸዋል

ህዳር 04፣2010

ትናንት በተለያዩ የአለም ከተሞች በተካሄዱ የሩጫ ውድድሮች ከ30 በላይ ኢትዮጵውያን አትሌቶች ድል ቀንቷቸዋል፡፡

በሻንጋይ ማራቶን በሴቶች ሮዛ ደረጀ እና ሂሩት ጥበቡ አንደኛ እና ሶስተኛ ደረጃ ይዘው አጠናቀዋል፡፡ ጉሉሜ ቶሎሳ አራተኛ ወጥታለች፡፡ በወንዶች ኢትዮጵያውያኑ 5ኛ፣ 7 ኛ እና 8ኛ ደረጃን ይዘዋል፡፡

በኢስታንቡል ማራቶን ደግሞ ባዙ ወርቁ በወንዶች፣ ለተብርሃን ሀይሌ በሴቶች ሶስተኛ ሆነዋል፡፡

በቤሩት ማራቶን ደግሞ አዳነ አምሳሉ በወንዶች ሁለተኛ፣ ሽታየ ሀብተገብርኤል እና  በቀለች ዳባ በሴቶች ሁለተኛ እና ሶስተኛ ሆነው አጠናቀዋል፡፡

በአቴንስ ማራቶንም በሴቶች በዳሩ ሂርፓ ቀዳሚ ሆና ስታጠናቅቅ ፣ በወንዶች ሱፋ ጫላ 8ኛ ወጥቷል፡፡

በኢስታቡል በተካሄደው የ15 ኪሎሜትር ሩጫ ውድድር በወንዶች አቤ ጋሻሁን፣ ሀይማኖት አለው እና ታየ ግርማ ከ1ኛ እስከ 3ኛ ያለውን ደረጃ ወስደዋል፡፡ በሴቶች ቃል ኪዳን ፈንቴ ሶስተኛ ወጥታለች፡፡

በስፔን በተካሄደው የአገር አቋራጭ ሩጫ ውድድር ደግሞ በወንዶች ጌታነህ ሞላ፣ በሴቶች ሰንበሬ ተፈሪ አሸናፊ ሆነዋል፡፡

ምንጭ፡-የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌደሬሽን 

Average (0 Votes)

ተያያዥ ዜናዎች ተያያዥ ዜናዎች