ፌደሬሽኑ 28ኛውን ሳምንት የወንዶች ፕሪሜየር ሊግ ጨዋታዎች እንዲራዘም ወሰነ

ግንቦት 01 ፣ 2009

በሳምንቱ  መጨረሻ ሊካሄዱ  የነበሩ የ28ኛ ሳምንት የወንዶች ፕሪሜየር ሊግ ጨዋታዎች ወደ ግንቦት 10፣ 2009 ዓ.ም እንዲዘዋወሩ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን ውሳኔ አሳለፈ።

ፌደሬሽኑ  ትላንት በሰጠው መግለጫ  ነው ጨዋታዎቹ  እንዲተላለፉ  ውሳኔ ማሳለፉን ያስታወቀው።

በውሳኔው መሰረት ሊጠናቀቅ የ3 የጨዋታ መርሃ ግብር በቀረው የኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ ጨዋታዎች  ሆን ተብሎ  ውጤት በመልቀቅ የጨዋታው ሂደት እንዳይጎዳ ለማድረግ ሁሉም ጨዋታዎች በተመሳሳይ ሰአት ይደረጋሉ፡፡

ውጤት የመልቀቅ ሁኔታ ከተፈጠረ ከ4 አስከ 5 ክለቦች ሊጎዱ እንደሚችሉም ነው በመግለጫው ላይ ፌድሬሽኑ የገለፀው ፡፡

የውድድሩ ሰዓት እና ቦታ ሰሞኑን ይፋ እንደሚያደርግ ፌድሬሽኑ አስታውቋል፡፡

ሪፖርተር ፥ ላሉ  ኢታላ 

Average (0 Votes)

ተያያዥ ዜናዎች ተያያዥ ዜናዎች