ጅማ ከተማ የ2009 የከፍተኛ ሊግ አሸናፊ ሆነ

ሃምሌ 12፤2009

ዛሬ በተካሄደው የ2009 አጠቃላይ የከፍተኛ ሊግ ጨዋታ ጅማ ከተማ ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲን 1ለ0 በማሸነፍ ባለድል መሆኑን አረጋግጧል፡፡

ጅማ ከተማ የምድብ ሀ አንደኛ ሆኖ ያጠናቀቀ ሲሆን ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ደግሞ የምድብ ለ አንደኛ ሆነው ማጠናቀቅ ችለው ነበር፡፡

የሁለቱን ቡድኖች አጠቃላይ አሸናፊ ለመለየት በተደረገው ጨዋታ ጅማ ከተማ አክለሲያስ ግርማ በ23ኛው ደቂቃ በፍጹም ቅጣት ምት ባስቆጠራት ግብ አሸናፊ መሆን ችለዋል፡፡

ጅማ ከተማ እና ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ በቀጥታ ፕሪሚየር ሊጉን መቀላቀል የቻሉ ቡድን ሲሆኑ መቀሌ ከተማ ደግሞ ሃዲያ ሆሳዕናን 2ለ1 በማሸነፍ ወደ ፕሪሚየር ሊጉ መቀላቀሉን ያረጋገጠ ቡድን መሆኑ የሚታወስ ነው፡፡

Average (0 Votes)

ተያያዥ ዜናዎች ተያያዥ ዜናዎች